Uncategorized

የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃግብር ማሳሰቢያ

የተወደዳችሁ የእመቤታችን የቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን አባላት በሙሉ፡፡

ለሜይ 2/2020 ታስቦ የነበረው የቤተክርስቲያናችን የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃግብር ላልተወሰነ ጊዜ የተራዘመ ሲሆን በተለይ በዚህ ጊዜ አብዝተን በጸሎት ቤተክርስቲያናችንን እንድናስባትና እግዚአብሄር ይህን የጨለማ ጊዜ ገፎልን በሰላም ከቁጥር ሳንጎድል ለመሰባሰብ ያብቃን፡፡

ወስብሃት ለእግዚአብሄር!!

የደብሩ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ