Past Events

 ያለፉ ትእይንተ ፕሮግራሞች

የክርስትና መስራቹ ራሱ መድኃኔዓለም ክርስቶስ ነው፡፡ (በማቴ 16፡18)“በዚህችም ዓለት ላይ ቤተክርስቲያኔን እሰራለሁ፡፡ የገሀነም በሮች ደጆችም አይበረቱባትን፤አይችሏትም”  በማለት ቤተክርስቲያን ማለትም ክርስቲያንነትን በሰው ልጅ ላይ እንደሚሰራ ዓለት እንደሆነ ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለስምዖን በራሱ ባለው በህያው ቃሉ አረጋግጦልናል፡፡ ክርስቲያኖች ክርስቲያን ከመባላቸው አስቀድሞ ምዕመናን (መዝ 100፡7) ፤ ደቀመዛሙርት (ኢሳ 8፡16) ፤ ወንድሞች (ማቴ 8፡10) የመሳሰሉት በመባል ይጠሩ ነበር፤ ነገር ግን ደቀመዛሙርቱ ክርስቲያን ተብለው ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰየሙት በአንጾኪያ በማርቆስ እናት በማርያም ቤት እንደነበር ቅዱስ መጽሀፍ ይነግረናል፡፡ (የሐዋ 11፡26)

የላይኛውን እንደ መግቢያ ካየነው፤ በቤተክርስቲያን ውስጥ ደሞ እለት ከእለት ከሚደረገው ሥርአተ-ቤተክርስቲያን ጎን ለጎን  እንደ ጌታችን ቃል መሰረትበምእመኑ ላይ ዓለት ለመስራት ስትል ቤተክርስቲያን የምታካሂዳቸውና ከዚህ በፊት ያካናወነቻቸው ብዙ መንፈሳዊ ክንውኖች አሉ። ላልፉት አምስት አመታት እንኩዋን በቤተክርስቲያናችን የተለያዩ መንፈሳዊ ጉባኤዎች፤ የፍቅር ማእዶች (አጋፔ)፤ ትእይንተ-ፕሮግራሞችና የቤተክርስቲያን አገልግሎቶች ሲደረጉ ከቆዩት መካከል ከሚጠቀሱት ጥቂቶቹ  ናቸው።

እነዚህ ፕሮግራሞች (ክንውኖች) ለምእመኑ በሚሰጡበት ጊዜ የሚያስገትን ጥቅሞች እንደሚከተለው በጥቂቱ ማየት ይቻላል። በፎቶ ማሳያው ያለውንም በመመልከት ስላለፉት አበይት ክንውኖች የበለጠ መረዳት ይችላሉ።

እግዚያብሔርን ለማወቅ
መቼም ዓለም አንድ መንደር በሆነችበት ዘመን ስለ እግዚያብሔር ያልሰማ አለ ብሎ ለመናገር ያስቸግራል፡፡ ይሁን እንጂከዕውቀት ብዛት እግዚአብሄርን የካዱ (እግዚአብሔር የለም) ያሉ በርካታ ሰዎች በምድራችን መኖራቸው ግልጽ ነው፡፡ይህም ስንፍና እንጂ እውቀት እንዳልሆነ ልበ አምላከ ቅዱስ ዳዊት ይነግረናል፡፡ “ይበል አብድ በልቡ አልቦእግዚአብሔር” ሰነፍ በልቡ እግዚአብሔር የለም ይላል (መዝ 13፡1)፡፡ ፍልስፍና ማለት ጥበብን ማፍቀር ማለት እንጂእግዚአብሄርን አለማወቅ ወይም መካድ ማለት አይደለም፡፡ አንድ ልጅ አባቱን አላውቅህም አባቴ አይደለህም ስላለውአባቱ አልወለደውም ማለት አይደለም እንዳውም ልጁ ሲጠራ አባቱን የካደ ልጅ ተብሎ ይጠራል፡፡
በዕምነት ለማደግ
ብዙዎች ክርስቲያን ተብለው ይጠራሉ ጥቂቶች ብቻ በእምነት ውስጥ በጥበብ ይኖራሉ፡፡ “ዕምነት ተስፋስለምናደርገው ነገር የሚያስረግጥ የማናየውንም ነገር የሚያስረዳ ነውና” (ዕብ11፡1) የሰው ልጅ በሃይማኖት ካልኖረለምኞቱ ገደብ የለውም፡፡ ያለኝ ይበቃኛል አይልም፡፡ አመንዝራ ሲያይ በፍትወት ስሜት ይቃጠላል፣ የወይን ጠጅ በብርሌባማረ መልኩ ባየ ጊዜ መጠጥ ያምረዋል ለዚህ እኮ ጥበበኛው ጠቢቡ ሰለሞን “ከተማን ከመግዛት ራስን መግዛትይበልጣል ያለው”
በእግዚአብሔር ፍቃድ ለመኖር
እግዚአብሔር ከእኔ ይልቅ ስለ እኔ ያስባል ብሎ ማመን ነው፡፡የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚያደርግ ለዘለዓለምይኖራል፡፡(የሐ2፡17) የጌታችንም ፈቃድ ሁሉ የእግዚአብሔር እንደሆነ ሲያስተምር “አባት ሆይ ብትፈቅድ ይህችን ጽዋከእኔ ውሰድ ነገር ግን የእኔ ፍቃድ አይሁን የአንተ እንጂ”(ሉቃ22፡42) ምክንያቱም ሀዋርያው እንደተናገረው ”ስለ በጎፈቃድ መፈለግንም ማድረግንም በእናንተ የሚሰራ እግዚአብሔር ነውና” እንዲል (ፊሊ1፡13)
እግዚአብሔርን ለመምሰል
ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህች ዓለም ሶስት ዓመት ከሶስት ወራት በአገልግሎት ሲቆይበርካታ ትምህርቶችን ከማስተማሩም በላይ በሕይወቱ አብነት ለመሆን መልካም ሥራ ካደረገ በኋላ ከመዝ ግበሩ  እናንተም እንዲሁ አድርጉ(ዮሐ13፡14)(ምንም እንኳን መልካምነት የባህርይው ቢሆንም) በማለት ክርስቲያኖችበሕይወት ዘመናቸው ክርስቶስን መምሰል እንዳለባቸው መጽሀፍ ይስተምረናል፡፡ሐዋሪያው ቅዱስ ጳውሎስም ይህንንቃል ”እኔ ክርስቶስን እንደምመስል እኔን ምሰሉ”(1ኛቆሮ 11፡1) በማለት ያረጋግጥልናል፡፡በመሆኑም የመንፈስን ፍሬበማድረግ የስጋን ሥራ በመተው አምላካችንን መምሰል ይገባናል ማለት ነው፡፡(ገላ 5፡18)ይህንን በማድረግ ቅዱሳንቅድስናን ገንዘብ አድርገዋል፡፡“እግዚአብሔር መምሰል ግን ለአሁኑ እና ለሚመጣው ተስፋ ስላለው ለነገር ሁሉይጠቅማል”(2ጢሞ 4፡8)
ፍቅር እንዲኖረን ለማድረግ
በክርስትና መጀመሩያውም መጨረሻውም ፍቅር ነው፡፡ ምክንያቱም “ፍቅር የሌለው እግዚአብሔርን አያውቅም፡፡እግዚአብሔር ፍቅር ነውና” (1ዮሐ 4፡8) በመሆኑም ያለ ፍቅር ክርስትና የለም፡፡ቢኖር እንኳን ቅ/ጳውሎስ እንደተናገረውከንቱ ነው “ሁሉ ቢኖረኝ ፍቅር ግን ከሌለኝ ከንቱ ነኝ”(1ቆሮ 13፡1)
ከመስቀሉ ለመካፈል
የጠፋውን በግ ፍልጋ ራሱን ባዶ ያደረገው ክርስቶስ (ፊሊ 2፡8) ድሉ በመስቀል ስለ ተጠናቀቀ ክርስቲያኖች በሕይወትዘመናቸው ከመስቀሉ ተካፋይ መሆን አለባቸው፡፡ ለዚህም ከመስቀሉ ስር የተሰጠችንን እናት ቅድስት ድንግል ማርያምንመውሰድ፤ የተቆረሰውን ቅዱስ ስጋ መብላት፤ የፈሰሰውን ክቡር ደም መጠጣት ይኖርብናል ማለት ነው፡፡ (ዮሐ 19፡27፤ዮሐ 6፤56) ይህ ሁሉ ሲሆን ለዘለዓለም በሕይወት እንኖራለን ማለት ነው፡፡

በደብረጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተክርስትያን ካገለገሉ የሃገራችን ሰባክያነ ወንጌል እና ዘማርያን መካከል እነዚህ ይገኙበታል፡፡
1/ መጋቤ ሐዲስ እሸቱ አለማየሁ (ከኢትዮጵያ)፤
2/ ዲ/ን ብርሃኑ አድማስ (ከኢትዮጵያ)፤
3/ ሙሃዘ ጥበባት ዲ/ን ዳንኤል ክብረት (ከኢትዮጵያ)፤
4/ ዲ/ን ዶ/ር መርሻ አለኽኝ (ከኢትዮጵያ)፤
5/ መምህር ዘላለም ወንድሙ (ከኢትዮጵያ)፤
6/ መምህር ምህረተዓብ አሰፋ (ከኢትዮጵያ)፤
7/ መላከሳሌም ቆሞስ አባ ገብረኪዳን (ከላስቭጋስ)፤
8/ ቀሲስ ደጀኔ ሽፈራው (ዴንቨር)፤
9/ዲ/ን ጎርጎሪዮስ ደጀኔ (ከዴንቨር)፤
10/በኩረመዘምራን ኪነጥበብ ወልደቂርቆስ (ከኢትዮጵያ)፤
11/ ሊቀመዘምራን ይልማ ሃይሉ (ከሚኒያፖሊስ)፤
12/ ቀሲስ ዘማሪ ምንዳዬ በሃኑ (ከኢትዮጵያ)፤
13/ ዘማሪት እግዚሃርያ ይልማ (ከሚኒያፖሊስ)፤
14/ ቀሲስ ዶ/ር መስፍን ተገኝ (ከኢትዮጵያ) ሲሆኑ ለአገልግሎታቸው በቤተክርስቲያናችን ስም እግዚአብሄር ይስጥልን፤ ቃለ ህይወት ያሰማልን እንላለን፡፡

ያለፉ አበይት ክንውኖችና ትእይንቶችን ማሳያ ከፎቶና ቪድዮ ጋር

Photo Album
IMG_8204
IMG_5447
e9e6232d-51d5-4eef-8796-f778d44152df
media-share-0-02-01-0da60282bab62c7ab1e8b7b58a9d2daedad3434fd82801afe5b2801e8530b168-796e4bc6-be69-413f-b7b5-4587d7e5aab1
IMG_8718
Youth conference (3)_add
media-share-0-02-01-ee78fe06677b29dad82a9f42355d2a0765c5e69136999ca512d44c72ac55d1c1-202cdea9-013e-490a-8130-7961c032244b
IMG_1210
Photo Album IMG_8204 IMG_5447 e9e6232d-51d5-4eef-8796-f778d44152df media-share-0-02-01-0da60282bab62c7ab1e8b7b58a9d2daedad3434fd82801afe5b2801e8530b168-796e4bc6-be69-413f-b7b5-4587d7e5aab1 IMG_8718 Youth conference (3)_add media-share-0-02-01-ee78fe06677b29dad82a9f42355d2a0765c5e69136999ca512d44c72ac55d1c1-202cdea9-013e-490a-8130-7961c032244b IMG_1210