ሳምንታዊ ትምህርት

ሳምንታዊ ትምህርት

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ፣ አሜን።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መሠረታዊ እምነት ለማስፋፋት ትምህርተ «ተዋሕዶ» ለምእመናኑ በየጊዜው ማዳረስ በጣም አስፈላጊ ነው። የተዋሕዶ ትምህርት በእለተ ቅዳሴ ብቻ በሚሰጡ ቃለ እግዚያብሄር ተዳሶ የሚያልቅ ሳይሆን የእለተ ተእለት መንፈሳዊ ምግባችን ሊሆን ይገባል።

ለዚህም ሲባል በዚህ ክፍል ውስጥ ካለው የምእመናኑ የህይወት ውጥረት ምክንያት በየእለቱ ትምህርት ማዳረስ ባይቻልም ነገር ግን ዘወትር በየሳምንቱ ቅዳሜ ቅዳሜ ከንድ ሰአት ያልበለጠ ተከታታይነት ያለው ትምህርት በዚህ ክፍል የሚሰጥ ይሆናል።

ይሁንና በዚህ ዝግጅት ግን እንደ ትምህርቱ ጥልቀትና ምጥቀት ሳይሆን፣ እንደ አዘጋጁ የዕውቀት ውሱንነትና እንደ ተቀባዩ የአእምሮ ስፋት መጠን፣ ግልጽ በሆነ አቀራረብ በየሳምንቱ ተከፋፍሎ ይቀርባል።

የቀጣዮቹ ትምህርቶች ርእስ ፡

ኦርቶዶክሳዊ – ቤተሰብ