ትምህርተ ሃይማኖት

(ምንጭ፡ በሊቀ ካህናት ኃይለሥላሴ ዓለማየሁ)

ወልድ ዋሕድ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንና የሌሎች አኃት አብያተ ክርስቲያናት መሠረታዊ እምነት «ተዋሕዶ» ነው። ተዋሕዶን የሚተረጉም ኃይለ ቃልም ፣ «ወልድ ዋሕድ» የሚለው ነው። ወልድ ዋሕድ ለሚለው ሥያሜ መሠረቱ «ቃል ሥጋ ኮነ» የሚለው ቃለ ወንጌል ነው። ዮሐ ፩፥fg።

ትምህርተ ሃይማኖት መለኮታዊ ምሥጢርን የሚያስረዳ እንደመሆኑ ትምህርቱ ጥልቅ፣ ረቂቅና ምጡቅ ነው። ይሁንና በዚህ ዝግጅት ግን እንደ ትምህርቱ ጥልቀትና ምጥቀት ሳይሆን፣ እንደ አዘጋጁ የዕውቀት ውሱንነትና እንደ ተቀባዩ የአእምሮ ስፋት መጠን፣ ግልጽ በሆነ አቀራረብ ባጭር ባጭሩ ይቀርባል።

የሃይማኖት ትርጉም
1. ሃይማኖት ምንድን ነው?

ሃይማኖት ወይም እምነት ማለት ማመን፤ መታመን፤ የፈጣሪን ሕልውና ማወቅ፤ ከሃሊነቱን፣ መግቦቱንና ቸርነቱን መረዳት፤ መለኮታዊ እውነታዎችን በትክክል መቀበል፤ በእግዚአብሔር መለኮታዊ ሥራ ፈጽሞ አለመጠራጠር፤ ጥርጥርን ከኅሊና ማስወገድ፤ ስለ ሰማያዊ ሕይወት ጽኑ ተስፋ ማድረግ በሚሉ አገላለጾች ይተረጐማል።

ሃይማኖት በረቂቅ ሐሳብ፣ በልብ ሰሌዳነት፣ የሚጻፍ የአእምሮ መጽሔት ነው። ሃይማኖት የኅሊና መሰላል በመሆኑ የዓለምን አስቸጋሪ ዳገት ይወጡበታል። ሃይማኖት የሕይወት መርከብ በመሆኑ ገፊውን ማዕበል ተቋቁመው ባሕሩን ይሻገሩበታል። ንጉሠ ሰማይ ወምድር እግዚአብሔርን ደስ ያሰኙበታል። ዕብ f™፥፮። ልክና መጠን፣ ወሰንና ዳርቻ የሌለው መለኮታዊ ባሕርይ የሚታየው፣ ሕልውናው ከሃሊነቱና መግቦቱ የሚታወቀው በሃይማኖት ነው።

ቅዱስ ጳውሎስ የሃይማኖትን ኃይል ሲተረጉም፦ «እምነትም ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የሚያስረግጥ፣ የማናየውን ነገር የሚያስረዳ ነው።»ይልና በመቀጠልም «ነአምር ከመ ተፈጥረ ዓለም በቃለ እግዚአብሔር። ዓለም በእግዚአብሔር ቃል እንደተፈጠረ እናውቃለን።» ብሎአል። ዕብ f™፥፩-፫። ሃይማኖት ፍጡርን ከፈጣሪው ጋር የሚያገናኝ የኅሊና መሰላል በመሆኑ ፍጡር የሃይማኖት መሰላሉና ድልድዩ ከተሰበረበት ወደ ፈጣሪው መድረስ ይሳነዋል፤ ሌላ መድረሻ ሌላ መንገድ ፈጽሞ የለውም።

የሃይማኖት ኃይል ልዩና ዕፁብ ድንቅ የሚያሰኘው፣ ምድራዊ ባለሥልጣን የማይገዛውን የሚገዛ፣ በዓይነ ሥጋ የማይታየውን የሚያሳይ፣ በእጅ የማይዳሰሰውን የሚዳስስ፣ በሥጋዊ ጥበብ የማይመረመረውን የሚመረምር ምሥጢር መሆኑ ነው። ማቴ f¥፥f¦።

ልዕልና ነፍስ /የነፍስ ልዕልና/ ክብረ ነፍስ የሚገኘው በሃይማኖት ነው፤ ከሃይማኖት ውጪ የሚሆነው ሁሉ ኃጢአትና በደል ነው። «ወኲሉ ዘይከውን ዘእንበለ አሚን ኃጢአት ወጌጋይ ውእቱ። በእምነት ያልሆነ ሁሉ ኃጢአትም፣ በደልም ነው።» ሮሜ fg፥©ª። የሚታይና የማይታይ፣ ግዙፍና ረቂቅ፣ ሁሉ ከማይታይ እንደሆነ ማለትም በመለኮታዊ ሥልጣን የተገኘ መሆኑን ያሳውቃል።

እግዚአብሔር ለፍጥረቱ ሁሉ መገኘት ምክንያት ሳይሻለት በከሃሊነቱ እምሀበአልቦ ፈጥሮታል። ይህን ማወቅ የሚያስችል ከሃይማኖት ውጪ ሌላ ጥበብ ፈጽሞ የለም። የሰው ልጅ የእግዚአብሔርን መንግሥት ወራሽ የመሆን ዕድል የሚያገኘው በሃይማኖት ብቻ ነው። በዓለም ያለውን ሥርዓት በቀላሉ በምሳሌነት ማየት ይቻላል፤ ይኸውም የአንድን ሰው ሃብትና ንብረት ለመውረስ በቀላሉ ባለመብት መሆን የሚቻለው የባለጸጋው ወይም የባለሀብቱ ልጅ ሆኖ መገኘት ሲቻል ነው። በእግዚአብሔር መንግሥትም በሃይማኖት ልጅነትን ካላገኙ የመንግሥቱ ወራሽ መሆን አይቻልም።

«እውነት እውነት እልሃለሁ፤ ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም።» እንዳለ ጌታ በቅዱስ ወንጌል። ዮሐ ፫፥፭።

«… ስለዚህ ከእንግዲህ ልጅ ነህ እንጂ ባሪያ አይደለህም። ልጅም ከሆንክ ደግሞ የእግዚአብሔር ወራሽ ነህ።» ገላ ፬፥፬-፯። ሃይማኖት በአማኙ ዘንድ ሦስት ነገሮች ተሟልተው እንዲገኙ ግድ ይላል። እነዚህም፦

፩. ትክክለኛ አረዳድ /እውነት/ ፪. የልብ ንጽሕና /ቅንነት/ ፫. መጥዎተ ርእስ፣ ማለትም ጥብዓት፣ ራስን መካድ፣ ራስን አሳልፎ ለሃይማኖት መገዛት ፈቃደ ሥጋን አሸንፎ መስቀልን መሸከም የሚሉ ናቸው። እነዚህ መሠረታዊ ነገሮች ያልተሟሉለት አማኝ ግብዝ ሃይማኖተኛ ይባላል።

ማስረጃ

«… እግዚአብሔር አንድ እንደሆነ ታምናለህ፤ መልካም ታደርጋለህ። አጋንንት ደግሞ ያምናሉ፤ ይንቀጠቀጡማል። …» ያዕ ፪፥fg-©¼። ማር ፭፥፯። ጌታም በቅዱስ ወንጌል እንዲህ ይለናል። «በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ የሚለኝ ሁሉ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም።» ማቴ ፯፥©™።

«ሕዝቡንም ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ጠርቶ፣ እንዲህ አላቸው፤ በኋላዬ ሊመጣ የሚወድ ቢኖር፣ ራሱን ይካድ። መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ።» ማር ፰፥Ãg። ሉቃ ፱፥©ª። ማቴ ፲፥ÃÆ፣ f¥፥©g።

«ወኅሊናሁሰ ለነፍስትነ ሞተ ያመጽእ ላእሌነ፤ ወሕሊናሁሰ ለመንፈስ ሰላመ ወሕይወተ ይሁብነ። የሥጋችን ፈቃድ ሞትን ያመጣብናል /ያስፈርድብናል/ የነፍሳችን ፈቃዱ ግን ሰላምን ከእግዚአብሔር ጋር አንድነትን ድኅነትን ይሰጠናል። እስመ ኅሊናሁ ለነፍስትነ ፀሩ ለእግዚአብሔር ውእቱ። የሥጋችን ፈቃዱ የእግዚአብሔር ጠላቱ ነውና ሞትን ያመጣብናል።» ሮሜ ፰፥፭-፰። የሃይማኖት ዓላማውና ግቡ፣ ሀልዎተ እግዚአብሔርን ማሳወቅና ፍጡር በፈጣሪው ሕግና ትእዛዝ እየተመራ ዘለዓለማዊ ክብር እንዲያገኝ ማድረግ ነው። ማቴ ©È፥Ãg።

ሀልዎተ እግዚአብሔርን ማወቅ ማለትም ቅድመ ዓለም የነበረ፣ በማዕከለ ዓለም ያለ፣ ዓለምን አሳልፎ የሚኖር፣ ፈጣሪ፣ መጋቢ ሠራዒ፣ በመለኮታዊ ባሕርዩ ጸንቶ የሚኖር፣ ለመንግሥቱ ሽረት፣ ለሕልውናው ኅልፈት የሌለበት አንድ ፈጣሪ፣ አንድ አምላክ መኖሩን አውቆ ማመን ማለት ነው።

«እስራኤል ሆይ ስማ፤ አምላክህ እግዚአብሔር አንድ እግዚአብሔር ነው።» ዘዳ ፭፥፬።

የማይታይና የማይመረመር፣ የማይገሰስና የማይዳሰስ፣ ሕያወ ባሕርይ እግዚአብሔር በከሃሊነቱ ሁሉን የፈጠረ፣ በመግቦቱ ሁሉን የሚያስተዳድር፣ በቸርነቱ ሁሉን የሚጠብቅ አምላክ በመሆኑ ለፍጥረቱ የሚታወቅበት ገጽታ አንዱ ይኸው ነው። ሁሉን የሚገዛ፣ ሁሉን የሚያስተዳድር በመሆኑ ይቅርታውና መግቦቱ በሁሉም ላይ ነው።

«እስመ ቅንየትከ ወምልክናከ ላዕለ ኲሉ፣ ይሬስየከ ትሣሃል ላዕለ ኲሉ። ማለት በሁሉ ላይ ያለ ሥልጣንህና አገዛዝህ ሁሉን ይቅር እንድትል ያደርግሃል።» እንዲል።

«… እርሱ በክፉዎችና በበጎዎች ላይ ፀሐይን ያወጣልና፤ በጻድቃንና በኃጢአተኞችም ላይ ዝናቡን ያዘንባልና።» ማቴ ፭፥ÑÈ።

በከሃሊነቱ ዓለምን የፈጠረ እግዚአብሔር የማይታይ፣ የማይመረመርና የማይዳሰስ፣ እንደሆነ ቢታወቅም፣ ባሕርዩ ከሚገለጽባቸው አያሌ መገለጫዎች ጥቂቶቹን በምሳሌነት መመልከት ይቻላል። እነሱም፦

፩. ፈጣሪ ፪. ከሃሊ ፫. ምሉእ ፬. ዘለዓለማዊ ፭. ቅዱስ ፮. ፍጹም ፯. ማእምር /አዋቂ/ ጥበበኛ የሚሉ ናቸው። እነዚህን በዝርዝር እንመለከታለን።
እግዚአብሔር ፈጣሪ ነው

ፈጣሪ ስንል የሌለን ወይም ያልነበረን ነገር በሥልጣኑና በከሃሊነቱ ያስገኘ፣ ዓለምን እምሀበአልቦ /ካለመኖር ወደ መኖር/ የፈጠረ ማለታችን ነው። ዓለምን እምሀበአልቦ ያስገኘ፣ በመለኮታዊ ሥልጣኑ የሚታየውንና የማይታየውን፣ ግዙፉንና ረቂቁን ፍጥረት ሁሉ የፈጠረ እግዚአብሔር ነው።

እግዚአብሔር ዓለምን /ፍጥረቱን/ ለመፍጠር ምክንያት የሆነው መለኮታዊ ሥልጣኑ ብቻ ነው፤ የፍጥረታት ሁሉ አስገኝ እግዚአብሔር በመሆኑም የፍጥረታት ሁሉ ጌታና ባለቤት እግዚአብሔር ነው። እግዚአብሔር ዓለምን ፈጥሮ እንዲሁ አልተወውም፤ በመግቦቱ ይጠብቀዋል፤ ይህን ዓለም ካለመኖር ወደ መኖር ያመጣ እግዚአብሔር ብቻ በመሆኑና በመለኮታዊ ሥልጣኑ መሳይ ተወዳዳሪ ስለሌለውም እግዚአብሔር አንድ አምላክ ይባላል።

እግዚአብሔር ዓለሙን ሲፈጥር፣ ይሁን ብሎ በቃሉ፣ በመለኮታዊ ሥልጣኑና በከሃሊነቱ ፈጠረው እንጂ ፍጥረታትን ለማስገኘት ሌላ አፍአዊ ምክንያት አላስፈለገውም። እንደዚህ ያለ መለኮታዊ ሥልጣን በሰማይም በምድርም ስለሌለ፣ እግዚአብሔር ብቻ ፈጣሪ እንዲባል ያደርገዋል። «ዓይናችሁን ወደ ላይ አንሥታችሁ ተመልከቱ፤ እነዚህን የፈጠረ ማን ነው? ሠራዊታቸውን በቊጥር የሚያወጣ እርሱ ነው። ሁሉንም በየስማቸው ይጠራቸዋል። በኃይሉ ብዛትና በከሃሊነቱ ብርታት አንድስ እንኳ አይታጣውም።» ይላል የእግዚአብሔር ቃል። ኢሳ ፵፥©¥። በእግዚአብሔር ረቂቅ ሥልጣንና ከሃሊነት የተፈጠረ ፍጥረት ሁሉ ሥርዓት ተሠርቶለት፤ ወሰን ተበጅቶለት ይኖራል። ከተሠራለት ሥርዓት አይወጣም፤ ከተደነገገለት ወሰን አያልፍም። ለይኩን ባለው መለኮታዊ ቃሉ እንደተፈጠረ ሁሉ፣ በመለኮታዊ ትእዛዙ ፀንቶ ይኖራል። መዝ ü፥፬-፱፣ ዮሐ ፩፥፫።

«እነሆ ተራሮችን የሠራ ነፋስንም የፈጠረ፣. . . ንጋትን ጨለማ የሚያደርግ፣ በምድርም ከፍታዎች ላይ የሚረግጥ፣ ስሙ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው።» አሞ ፬፥fª። «ሰማያትን የፈጠረ እግዚአብሔር፣ እርሱም ምድርን የሠራና ያደረገ፤ ያፀናትም፣ መኖሪያ ልትሆን እንጂ ለከንቱ እንድትሆን ያልፈጠራት አምላክ እንዲህ ይላል። . . . ይናገሩ፤ ይቅረቡም፤ በአንድነትም ይማከሩ፤ ከጥንቱ ይህን ያሳየ ከቀድሞስ የተናገረ ማን ነው? ያሳየሁም፣ የተናገርሁም እኔ እግዚአብሔር አይደለሁምን? ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ የለም። እኔ ጻድቅ አምላክና መድኃኒትም ነኝ ከእኔም በቀር ማንም የለምና ወደ እኔ ዘወር በሉ ትድኑማላችሁ። ኢሳ ÑÈ፥fÆ-©¼።

በዓለም ታላቁ መጽሐፍ በመባል የሚታወቀው መጽሐፍ ቅዱስ ጽሑፉን የሚጀምርልን የሰማይና የምድር ፈጣሪ እግዚአብሔር መሆኑን በማረጋገጥ ነው። ዘፍ ፩፥፩፣ ዮሐ ፩፥፫፣ መዝ ü፥፮። ሰማይና ምድር ሲባልም፣ በሰማይና በምድር ያለውን ሁሉ፣ የሚታየውንና የማይታየውን፣ በሰው ዘንድ የታወቀውንና ገና ያለተደረሰበትን ፍጥረት ሁሉ አጠቃልሎ የያዘ ነው። ለዚህም ሁሉ ፈጣሪውና አስገኚው እግዚአብሔር በመሆኑ ዓለም የእግዚአብሔር ፍጥረት በመባል ይታወቃል። ዮሐ ፩፥፫፣ ቆላ ፩፥f¥።

ማንኛውም የሥራ ውጤት ያለ ሠራተኛ ሊገኝ እንደማይችል ሁሉ፣ ማንኛውም ፍጡር ያለፈጣሪ አልተገኘም። ምሳሌውን እንመልከት። በባሕር ላይ የሚንሳፈፉ ግዙፋን መርከቦች፣ ከባዱንና ቀላሉን ሸክም ችለው፣ ሕዋውን እየቀዘፉ በሰማይ የሚበሩ አውሮፕላኖች፣ ውስብስቡን የዓለም ምሥጢር በትንሽ አካሉ አከማችቶ የያዘ ኮምፒውተር፣ በአጠቃላይ ዕፁብ ድንቅ የሚባሉ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ሁሉ የሰው ልጅ አእምሮ ተጨንቆ ተጠብቦ ያስገኛቸው የጥበብ ውጤቶች እንጂ በራሳቸው የተገኙ አይደለም። ታዲያ ከላይ የተጠቀሱ የሰው ልጅ መገልገያዎች በራሳቸው መገኘት የሚችሉ ካልሆነ እነዚህን ያስገኘ ረቂቅ የሰው ልጅ አእምሮ እንዴት ያለ ፈጣሪ ሊገኝ ይችላል ተብሎ ሊታሰብ ይችላል!!! ፈጽሞ አይታሰብም። ከታሰበም አስተሳሰቡ የስንፍና ውጤት ይሆናል። ለዚሁም ነው፣ «ሰነፍ በልቡ እግዚአብሔር የለም ይላል።» ተብሎ የተጻፈው። መዝ fª፥፩፣ ኢሳ ÑÈ፥f™።

እግዚአብሔር ከሃሊ ነው

ከሃሊ ማለት ሁሉን የሚችል፣ በፍጡር ዘንድ ፈጽሞ የማይቻልን ሁሉ ማድረግ የሚችል፣ ለችሎታው ወሰንና ገደብ የሌለበት፣ ይህን ይችላል ያን ግን አይችልም የማይባል ፍጹም ከሃሊ ማለት ነው። እግዚአብሔር፣ ሁሉም ነገር ከሥልጣኑ በታች በመሆኑ ሁሉም ይቻለዋል።

ይህን አስመልክቶ በዕብራይስጡ ቃል «ኤልሻዳይ» ተብሎ ተሰይሟል፤ ሁሉን የሚችል ማለት ነው። እግዚአብሔር ለአብራም በተገለጠለት ጊዜ፣ ከሃሊነቱን በሚያረጋግጥ ቃል እንደተገለጠለት መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ በማለት ያስተምረናል። «አብራምም የዘጠና ዘጠኝ ዓመት ሰው በሆነ ጊዜ እግዚአብሔር ለአብራም ተገለጠለትና፦ እኔ ኤልሻዳይ ነኝ፤ በፊቴ ተመላለስ፤ ፍጹምም ሁን። ቃል ኪዳኔንም በእኔና በአንተ መካከል አደርጋለሁ፤ እጅግም አበዛሃለሁ አለው።» ዘፍ f¦፥፩።

ፍጹም ከሃሊነት የእግዚአብሔር መለኮታዊ ሥልጣን በመሆኑ እግዚአብሔር ፍጹም ከሃሊ ይባላል። «በውኑ ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር አለን? የዛሬ ዓመት ወደ አንተ እመለሳለሁ ሣራም ልጅን ታገኛለች።» ዘፍ fÆ፥fg። «. . . ይህ በሰው ዘንድ አይቻልም፤ በእግዚአብሔር ዘንድ ግን ሁሉ ይቻላል አላቸው። ማቴ fæ፥©È-©¥። ሉቃ ፩፥ÃÈ-ÃÆ።

እግዚአብሔር በሁሉ ምሉእ ነው
ምሉእ ማለት፣ ፍጹም የሆነ፣ ጉድለት /ሕፀፅ/ የሌለበት፣ በጊዜና በቦታ የማይወሰን፣ መቼም መች የነበረ ያለና የሚኖር ማለት ሆኖ የዚህ ባሕርይ ባለቤትም እግዚአብሔር ብቻ ነው።

እግዚአብሔር ከሁሉ በላይ ልዕልና ያለው አምላክ በመሆኑ ልዕልናውን ለመግለጽ ሲባል በሰማይ ያለ፣ ሰማያዊ አምላክ፣ ሰማያዊ አባት እየተባለ ይጠራል። ማቴ ፮፥፱-፲፣ fÆ፥፲።

እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ይወስናል እንጂ ሰማይና ምድር እግዚአብሔርን አይወስኑም። ከፍታዎችና ጥልቆች ሁሉ በእግዚአብሔር መዳፍ ናቸው፤

ማስረጃ

«ከመንፈስህ ወዴት እሄዳለሁ፤ ከፊትህስ ወዴት እሸሻለሁ፤ ወደ ሰማይ ብወጣ፣ አንተ በዚያ ነህ፤ ወደ ሲኦልም ብወርድ በዚያ አለህ። እንደ ንሥር የንጋትን ክንፍ ብወስድ እስከ ባሕርም መጨረሻ ብበር በዚያ እጅህ ትመራኛለች፤ ቀኝህም ትይዘኛለች። በውኑ ጨለማ ትሸፍነኛለች ብል፣ ሌሊት በዙሪያዬ ብርሃን ትሆናለች።» መዝ êëÆ፥፯-f¼።

«እኔ የቅርብ አምላክ ነኝ እንጂ የሩቅ አምላክ አይደለሁም። ሰው በስውር ቢሸሸግ፤ እኔ አላየውምን? ሰማይንና ምድርንስ የሞላሁ እኔ አይደለሁምን? ይላል እግዚአብሔር።» ኤር ©ª፥©ª።

«የእግዚአብሔርን ጥልቅ ነገር /ምሥጢር/ ልትመረምር ትችላለህን? ወይስ ሁሉን የሚችል አምላክን ፈጽመህ ልትመረምር ትችላለህን? ከሰማይ ይልቅ ከፍ ይላል፤ ምን ልታደርግ ትችላለህ? ከሲኦልም ይልቅ ይጠልቃል፤ ምን ልታውቅ ትችላለህ? ርዝመቱ ከምድር ይልቅ ይረዝማል፤ ከባሕርም ይልቅ ይሰፋል።» ኢዮ f™፥፯-፱።

«ውኆችን በእፍኙ የሰፈረ፣ ሰማይንም በስንዝር የለካ የምድርንም አፈር በመስፈሪያ ሰብስቦ የያዘ፣ ተራሮችን በሚዛን፣ ኮረብቶችንም በሚዛኖች የመዘነ ማነው? . . . እነሆ አሕዛብ በገንቦ እንዳለች ጠብታ ናቸው። . . . አሕዛብ ሁሉ በፊቱ እንዳልነበሩ ናቸው። ከምናምን እንደሚያንሱ እንደ ከንቱ ነገርም ይቈጥራቸዋል። እንግዲህ እግዚአብሔርን በማን ትመስሉታላችሁ? ወይስ በምን ምሳሌ ታስተያዩታላችሁ? . . .።» ኢሳ ፵፥f¼-fÆ።

እግዚአብሔር ዘለዓለማዊ ነው

ዘለዓለማዊ የሚለው ቃል ከቋንቋነቱ አኳያ ሲታይ የእግዚአብሔርን ባሕርይ ለመግለጽ ደካማ ወይም አናሳ ቃል ሆኖ የሚታይ ይመስላል።

በእርግጥም የቃሉ ገላጭነት የደከመ ወይም የጠበበ ነው። ይሁንና ሌሎች ቃላት ቢሆኑም የእግዚአብሔርን መለኮታዊ ባሕርይ በፍጹምነት የመግለጽ ብቃት አላቸው ብሎ መገመት አስቸጋሪ መሆኑ አይቀርም።

የሆነ ሆኖ ግን ዘለዓለማዊ ከሚለው ቃል መረዳት የሚቻለው፣ እግዚአብሔር አምላክ ቅድመ ዓለም የነበረ፣ በማዕከለ ዓለም ያለ፣ ዓለምን አሳልፎ የሚኖር፣ ፍጻሜ /መጨረሻ/ መነሻና መድረሻ የሌለው፣ እርሱ ራሱ መጀመሪያና መጨረሻ፣ የሆነ፣ የነበረ፣ ያለና የሚኖር ኅልፈትና ሽረት የሌለበት አምላክ መሆኑን ነው።

ማስረጃ

«ተራሮች ሳይወለዱ፥ ምድርም፥ ዓለምም ሳይሠሩ፥ ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ድረስ አንተ ነህ።» መዝ îæ፥፪።

«የእስራኤል ንጉሥ እግዚአብሔር፣ የሚቤዥም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እኔ ፊተኛ ነኝ እኔም ኋለኛ ነኝ፥ ከእኔ ሌላም አምላክ የለም።» ኢሳ Ñg፥፮።

«ሙሴም አግዚአብሔርን፦ እነሆ እኔ ወደ እስራኤል ልጆች በመጣሁ ጊዜ የአባቶቻችሁ አምላክ ወደ እናነተ ላከኝ ባልሁም ጊዜ ስሙስ ማነው ባሉኝ ጊዜ ምን እላቸዋለሁ? አለው። እግዚአብሔርም ሙሴን ያለና የሚኖር እኔ ነኝ አለው።» ዘጸ ፫፥fª።

«ያለውና የነበረው የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ አልፋና ዖሜጋ እኔ ነኝ ይላል።» ዮሐ ራእ ፩፥፰።

እግዚአብሔር ቅዱስ ነው
ቅዱስ ማለት ልዩ፣ ንጹሕ፣ ጽሩይ፣ ከክፉ ነገር ከረከሰ ነገር ሁሉ የተለየ ማለት ነው። እንደዚህ ያለ ቅድስና የባሕርይ ገንዘቡ የሆነ እግዚአብሔር ብቻ ነው። ሌላው ፍጥረት ቅዱስ ቢባል ቅድስና ከእግዚአብሔር ስለሚሰጠው ነው። እግዚአብሔር ግን ከሌላ የሚያገኘው፣ የሚጨመርለት ወይም የሚቀነስበት አንድም ነገር ፈጽሞ የለም። ፍጡርንና ፈጣሪን በአንድ ዓይነት አገላለጽ «ቅዱስ» እያልን ስንጠራ የቋንቋ እጥረት ሊሆን ይችላል እንጂ ባሕርየ ፈጣሪ ከባሕርየ ፍጡር ፈጽሞ የተለየ በመሆኑ የእግዚአብሔር ቅድስናም ከፍጡር ቅድስና ልዩ ነው። የተሻለ ስፋት ያላቸው አንዳንድ ቋንቋዎችም በፍጡርና በፈጣሪ መካከል ያለውን የቅድስና ልዩነት ለይተው ይጠቀማሉ። ባጭር አገላለፅ ባሕርየ ፍጡር /የፍጡር ባሕርይ/፦
  • ጽድቅና ኃጢአት
  • እውነትና ሐሰት
  • ትሕትናና ትዕቢት
  • ክፋትና ደግነት
  • ሕይወትና ሞት
  • ሹመትና ሽረት
  • ፍትሐዊነትና ፍትሕ አልቦነት
  • ርኅራኄና ጭካኔ
  • ፍቅርና ጥላቻ
  • ቁጣና ትዕግሥት ወዘተ… እየተፈራረቁበት ሲወድቅ ሲነሳ የሚኖር ሕይወት ነው። ፍጡር በአብዛኛው ጊዜ በእግዚአብሔር ቸርነትናመግቦት የሚኖር በመሆኑ ቅድስናው የእግዚአብሔር ምሕረት ታክሎበት የሚገኝ ካልሆነ አስቸጋሪ ይሆናል።

«ንጹሕ ይሆን ዘንድ ሰው ምንድን ነው? ጻድቅስ ይሆን ዘንድ ከሴት የተወለደ ምንድን ነው? እነሆ በቅዱሳኑ ስንኳ አይታመንም ሰማያትም በፊቱ ንጹሐን አይደሉም። ይልቁንስ አስጸያፊና የረከሰ፥ ኃጢአትንም እንደ ውኃ የሚጠጣ ሰው ምንኛ ያንስ?» ኢዮ fÈ፥fg-f¥።

ማስረጃ

«ንጉሡ ዖዝያን በሞተበት ዓመት እግዚአብሔርን በረጅምና ከፍ ባለ ዙፋን ላይ ተቀምጦ አየሁት፥ የልብሱም ዘርፍ መቅደሱን ሞልቶት ነበር። ሱራፌልም ከእርሱ በላይ ቆመው ነበር፥ ለእያንዳንዱም ስድስት ክንፍ ነበረው በሁለት ክንፍ ፊቱን ይሸፍን ነበር፥ በሁለቱም ክንፍ እግሮቹን ይሸፍን ነበር፥ በሁለቱም ክንፍ ይበር ነበር። አንዱም ለአንዱ፦ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ምድር ሁሉ ከክብሩ ተሞልታለች እያለ ይጮህ ነበር።» ኢሳ ፮፥፩-፫።

«እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ ለእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ እንዲህ በላቸው፦ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ቅዱስ ነኝና እናንተ እቅዱሳን ሁኑ።» ዘሌ fæ፥፩-፪። «ዳሩ ግን፦ እኔ ቅዱስ ነኝና ቅዱሳን ሁኑ ተብሎ ስለተጻፈ የጠራችሁ ቅዱስ እንደሆነ እናንተ ደግሞ በኑሮአችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ።» ፩ኛ ጴጥ ፩፥f¥።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንም በቅዱሳን አባቶች በቅዱስ ያሬድና በአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ አማካይነት ከእግዚአብሔር ባገኘችው ጸጋና በረከት በማሕሌትዋ፣ በሰአታትዋና በቅዳሴዋ እንደ መላእክት ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር… እያለች ዘወትር ፈጣሪዋን ታመሰግናለች።

ማስረጃ

  • «ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ሕያው ዘኢይመውት።»
  • «ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር ጸባዖት ፍጹም ምሉእ ሰማያተ ወምድረ ቅድሳተ ስብሐቲከ።»
  • «ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር ዘእምቅድመ ዓለም ሀሎ ወይሄሉ እስከ ለዓለም።»
  • «ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር ዘይሴባሕ እምትጉሃን ወይትቄደስ እምቅዱሳን።»
  • «ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር የአማልክት አምላክ ዘወትር /ሁልጊዜ/ በሰማይና በምድር ያለ፤ የሚኖር።»
ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን እንዲህ ዓይነቱ የማያቋርጥ ምስጋናዋ ከቅዱሳን መላእክት ተርታ ሊያሰልፋት ችሏል።
እግዚአብሔር ፍጹም ነው

ፍጹምነት የእግዚአብሔር ልዩ የባሕርይ ገንዘብ ነው። ፍጹም ማለትም በሁሉ ዘንድ በሁሉ አቅጣጫ የሚገኝ ሕፀፅ /ጉድለት/ የሌለበት፣ ነውር የማይገኝበት፣ በሁሉም የመላ፣ የተካከለ፤ መሳይ፣ ተመሳሳይ፣ አምሳያ የማይገኝለት፤ ኃያል፣ አሸናፊ፣ መጋቢ ሠራዒ፣ ሁሉን የሚገዛ፣ ወዘተ….. ማለት ነው።

የባሕርይ ፍጹምነት የእግዚአብሔር የግል ገንዘቡ በመሆኑ እንደ እግዚአብሔር ያለ በፍጹምነት የሚገኝ ማንም የለም።

«እግዚአብሔር በመንገዱ ሁሉ ምስጉን ነው። የአማልክት አምላክ ፍጹም አሸናፊ ነው። የሌለበት ጊዜ የለም፤ የታጣበትም ጊዜ የለም። በመለኮቱ ግን ፈጽሞ የታየበት ጊዜ የለም። እርሱን ማየት የሚችል የለም። አነዋወሩም እንደምን እንደሆነ የሚያውቅ /ማወቅ የሚችል/ የለም።» እንዳሉ ûüýÆ አበው ርቱዓነ ሃይማኖት /ቅዳሴ ዘሠለስቱ ምእት/።

«አነሆ እግዚአብሔር ታላቅ ነው፥ እኛም አናውቀውም [መርምረን አንደርስበትም]። የዘመኑም ቁጥር አይመረመርም።» ኢዮ Ã¥፥©¥።
እግዚአብሔር ፍጹም ነው

ፍጹምነት የእግዚአብሔር ልዩ የባሕርይ ገንዘብ ነው። ፍጹም ማለትም በሁሉ ዘንድ በሁሉ አቅጣጫ የሚገኝ ሕፀፅ /ጉድለት/ የሌለበት፣ ነውር የማይገኝበት፣ በሁሉም የመላ፣ የተካከለ፤ መሳይ፣ ተመሳሳይ፣ አምሳያ የማይገኝለት፤ ኃያል፣ አሸናፊ፣ መጋቢ ሠራዒ፣ ሁሉን የሚገዛ፣ ወዘተ….. ማለት ነው።

ፍጹምነት የእግዚአብሔር ልዩ የባሕርይ ገንዘብ ነው። ፍጹም ማለትም በሁሉ ዘንድ በሁሉ አቅጣጫ የሚገኝ ሕፀፅ /ጉድለት/ የሌለበት፣ ነውር የማይገኝበት፣ በሁሉም የመላ፣ የተካከለ፤ መሳይ፣ ተመሳሳይ፣ አምሳያ የማይገኝለት፤ ኃያል፣ አሸናፊ፣ መጋቢ ሠራዒ፣ ሁሉን የሚገዛ፣ ወዘተ….. ማለት ነው።

የባሕርይ ፍጹምነት የእግዚአብሔር የግል ገንዘቡ በመሆኑ እንደ እግዚአብሔር ያለ በፍጹምነት የሚገኝ ማንም የለም።

«እግዚአብሔር በመንገዱ ሁሉ ምስጉን ነው። የአማልክት አምላክ ፍጹም አሸናፊ ነው። የሌለበት ጊዜ የለም፤ የታጣበትም ጊዜ የለም። በመለኮቱ ግን ፈጽሞ የታየበት ጊዜ የለም። እርሱን ማየት የሚችል የለም። አነዋወሩም እንደምን እንደሆነ የሚያውቅ /ማወቅ የሚችል/ የለም።» እንዳሉ ûüýÆ አበው ርቱዓነ ሃይማኖት /ቅዳሴ ዘሠለስቱ ምእት/።

«አነሆ እግዚአብሔር ታላቅ ነው፥ እኛም አናውቀውም [መርምረን አንደርስበትም]። የዘመኑም ቁጥር አይመረመርም።» ኢዮ Ã¥፥©¥።

ማእምር

ማእምር ማለት ሁሉን የሚያውቅ፣ ሁሉን የሚረዳ፣ ድርሱን፣ ርግጡን፣ ልኩን የሚያውቅ ወይም ያወቀ ማለት ነው።

ዕውቀት ከባሕርይና ከትምህርት ይገኛል። የትምህርት ዕውቀት ማለትም ያልለመዱትን ነገር መልመድ፣ መረዳት፣ መገንዘብ ማለት ነው። ከትምህርት የሚገኝ ዕውቀት ከትንሽ ወደ ትልቅ፣ ግልጽ ከሆነ መነሻና መድረሻ ወደማይገኝለት ወይም ፍጻሜ ወደ ሌለው ውስብስብ ነገር አያደገ፣ እየመጠቀና እየረቀቀ የሚሔድ ልምድ ነው። ሌላው ማወቅ የሚባለው ደግሞ አንድን ነገር ከመሆኑ በፊት፣ በሆነ ጊዜና ከሆነም በኋላ ያለውን ነገር ያመለክታል።

እንዲህ ያለው ዕውቀት ፍጡር ከፈጣሪ በተሰጠው አእምሮ መሠረት የሚያገኘው ክሂሎት /ችሎታ/ ይባላል። ሀብተ ትንቢት የተሰጣቸው የእግዚአብሔር ሰዎችም መጻእያትንና ሐላፊያትን አውቀው ትንቢት ይናገራሉ፣ ያስተምራሉ።

ከባሕርይ የሚገኝ ዕውቀት ደግሞ አስተማሪ፣ መካሪ፣ አዘካሪ ወይም አስታዋሽ ሳያስፈልግ በተፈጥሮ ማለትም በአእምሮ ጠባይዕ የሚገኝ ከእግዚአብሔር የተሰጠ ጸጋ ነው። በአጠቃላይ ፍጡር የሆነውን ነገር አይቶ ሰምቶ፣ ተምሮ ተመራምሮ ያውቃል፤ ሐላፊያትን መጻእያትንም እንደ ቅዱሳን ነቢያት መንፈስ እግዚአብሔር ገልጾለት /አናግሮት/ ያውቃል ይናገራል ይመሰክራል። ኢሳ. ፯፥fg፣ ፱፥፮። የፍጡር ዕውቀት ሁሉም በዓረፍተ ዘመን የተገደበ ነው፤ ገደብ የሌለው የፍጡር ዕውቀት ፈጽሞ የለም። መገኛውም እግዚአብሔር ነው።

የእግዚአብሔር ዕውቀት ከዚህ ሁሉ ፈጽሞ የተለየ ነው። ነገሮች ሁሉ ከመታሰባቸው፣ ፍጥረታት ሁሉ ከመፈጠራቸው፣ መጻእያት ሁሉ ከመድረሳቸው /ከመሆናቸው/፣ ሓላፊያት ሁሉ ካለፉ ከጠፉ በኋላ በሕሊና አምላክ አሉ፤ በእግዚአብሔር ዘንድ ይታወቃሉ። የእግዚአብሔርን ዕውቀት ሊገድብ የሚችል ምንም ዓይነት ምክንያት የለም።

ማስረጃ

«ውእቱሰ የአምር ሕሊና ሰብእ እምቅድመ ኵነታ።»

«ልብንና ጥልቅንም መርምሮ ያውቃቸዋል ምክራቸውንም ሁሉ ያውቃል እግዚአብሔር የልቡና አሳብን ሁሉ ያውቃል… ያለፈውንም የሚመጣውን እሱ ይናገራል የተሠወረውንም ምሥጢር ይገልጣል። ከእግዚአብሔር ምክር ሁሉ የሚያመልጥ የለም ከነገሩ ሁሉ አንዲት ቃል ስንኳ የሚሰወረው የለም።» ሲራ Ѽ፥fÆ-፳።

«አቤቱ መረመርኸኝ፥ አውቅኸኝም። አንተ መቀመጤንና መነሳቴን አወቅህ አሳቤን ሁሉ ከሩቅ አስተዋልህ። ፍለጋዬንና ዕረፍቴን አንተ መረመርህ መንገዶቼን ሁሉ ቀድመህ አወቅህ፥… አቤቱ፥ አንተ እነሆ የቀድሞውንና የኋላውን አወቅህ… እውቀትህ ከእኔ ይልቅ ተደነቀች በረታች፥ ወደ እርስዋም ለመድረስ አልችልም።» መዝ êëÆ፥፩-፮።

«ነገር ግን ኢየሱስ ሰዎችን ሁሉ ያውቅ ነበር ስለ ሰውም ማንም ሊመሰክር አያስፈልገውም ነበርና አይተማመናቸውም ነበር ራሱ በሰው ያለውን ያውቅ ነበርና።» ዮሐ ፪፥©È፣፮፥#g፤ ማቴ ፱፥፬።

2. ክርስቲያናዊ ህይወት

ክርስትና የሚለው ቃል “XPIETIAVOS” ኽርስቲያኖስ ከሚለው የግሪክ ቃል የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም የክርስቶስ መሆን ማለት ነው፡፡ ክርስትና ሰዎች በፍቅረ እግዚአብሔር ተስበው፤ ፈጣሪያቸውን አውቀው፤ እረፍትን ሽተው፤ በህጉና በትእዛዙ ፀንተው፤ ለመኖር ሲሉ ከዓለም ፈቃድ ተለይተው የሚኖሩበት ህይወት ነው፡፡ ይህንንም ኢየሱስ ይወደው የነበረው ደቀመዝሙር ዮሐንስ “ዓለምን ወይም በዓለም ያሉትን አትውደዱ በዓለም ያለው ሁሉ እርሱም የስጋ ምኞትና የዓይን አምሮት ስለገንዘብም መመካት ከዓለም ስለሆነ እንጂ ከአባት ስላልሆነ÷ ማንም ዓለምን ቢወድ የአባት ፍቅር በእርሱ ውስጥ የለም፡፡

ዓለሙም ምኞቱም ያልፋሉ የእግዚያብሔርን ፈቃድ የሚያደርግ ግን ለዘለዐለም ይኖራል” (1ዮሐ 2፡16) በማለት ክርስቲያን ለመሆን በመጀመሪያ ዓለምን መካድ እንዳለብን ያስተምረናል፡፡ በክርስትና ወድቆ (ተረግሞ) የነበረው የሰው ዘር እንደ ተነሳ (እንደ ተፈታ)፤ የታመመው እንደ ተፈወሰ፤ የረከሰው እንደ ተቀደሰ፤ የሞተው እንደተነሳ፤የተሰበረው እንደተጠገነ፤ የሳተው እንደ ተመለሰ ይታመናል፡፡

የክርስትና መስራቹ ራሱ መድኃኔዓለም ክርስቶስ ነው፡፡ “በዚህችም ዓለት ላይ ቤተክርስቲያኔን እሰራለሁ፡፡ የገሀነም ደጆችም አይችሏት” (ማቴ 16፡18) በማለት ቤተክርስቲያን ሳይሆን ቤተክርስቲያኔን የራሱ እንደሆነች በህያው ቃሉ አረጋግጦልናል፡፡

ክርስቲያኖች ክርስቲያን ከመባላቸው አስቀድሞ ምዕመናን (መዝ 100፡7) ፤ ደቀመዛሙርት (ኢሳ 8፡16) ፤ ወንድሞች (ማቴ 8፡10) የመሳሰሉት በመባል ይጠሩ ነበር፤ ነገር ግን ደቀመዛሙርቱ ክርስቲያን ተብለው ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰየሙት በአንጾኪያ በማርቆስ እናት በማርያም ቤት እንደነበር ቅዱስ መጽሀፍ ይነግረናል፡፡ (የሐዋ 11፡26)

በምድራችን በሺዎች የሚቆጠሩ ሃይማኖቶች ይገኛሉ፡፡ የሃይማኖታቸውን መስራች ስናጠና ግን ሰዎች ሆነው እናገኛለን፡፡ ትምህርታቸው ዛሬም በተከታዮቻቸው ይኑር እንጂ እነርሱ ግን በህይወት የሉም፤ የክርስትና ዋና መስራች ግን ትናንት የነበረ ዛሬም ያለ ወደፊትም ዓለምን አሳልፎ የሚኖር ዐልፋና ዖሜጋ ዘዓአለማዊ በመሆኑ ዛሬም ስራውን አላቆመም ማለት ነው፡፡ ክርስቲያናዊ ህይወት ለመኖር ክርስቲያኖች የሚከተለውን መተግበር እንዳለብን የህይወት ምንጭ የሆነው መጽሀፍ ቅዱስ ያስተምረናል፡፡

ክርስቲያናዊ ህይወት

ክርስትና የሚለው ቃል “XPIETIAVOS” ኽርስቲያኖስ ከሚለው የግሪክ ቃል የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም የክርስቶስ መሆን ማለት ነው፡፡ ክርስትና ሰዎች በፍቅረ እግዚአብሔር ተስበው፤ ፈጣሪያቸውን አውቀው፤ እረፍትን ሽተው፤ በህጉና በትእዛዙ ፀንተው፤ ለመኖር ሲሉ ከዓለም ፈቃድ ተለይተው የሚኖሩበት ህይወት ነው፡፡ ይህንንም ኢየሱስ ይወደው የነበረው ደቀመዝሙር ዮሐንስ “ዓለምን ወይም በዓለም ያሉትን አትውደዱ በዓለም ያለው ሁሉ እርሱም የስጋ ምኞትና የዓይን አምሮት ስለገንዘብም መመካት ከዓለም ስለሆነ እንጂ ከአባት ስላልሆነ÷ ማንም ዓለምን ቢወድ የአባት ፍቅር በእርሱ ውስጥ የለም፡፡

ዓለሙም ምኞቱም ያልፋሉ የእግዚያብሔርን ፈቃድ የሚያደርግ ግን ለዘለዐለም ይኖራል” (1ዮሐ 2፡16) በማለት ክርስቲያን ለመሆን በመጀመሪያ ዓለምን መካድ እንዳለብን ያስተምረናል፡፡ በክርስትና ወድቆ (ተረግሞ) የነበረው የሰው ዘር እንደ ተነሳ (እንደ ተፈታ)፤ የታመመው እንደ ተፈወሰ፤ የረከሰው እንደ ተቀደሰ፤ የሞተው እንደተነሳ፤የተሰበረው እንደተጠገነ፤ የሳተው እንደ ተመለሰ ይታመናል፡፡

የክርስትና መስራቹ ራሱ መድኃኔዓለም ክርስቶስ ነው፡፡ “በዚህችም ዓለት ላይ ቤተክርስቲያኔን እሰራለሁ፡፡ የገሀነም ደጆችም አይችሏት” (ማቴ 16፡18) በማለት ቤተክርስቲያን ሳይሆን ቤተክርስቲያኔን የራሱ እንደሆነች በህያው ቃሉ አረጋግጦልናል፡፡

ክርስቲያኖች ክርስቲያን ከመባላቸው አስቀድሞ ምዕመናን (መዝ 100፡7) ፤ ደቀመዛሙርት (ኢሳ 8፡16) ፤ ወንድሞች (ማቴ 8፡10) የመሳሰሉት በመባል ይጠሩ ነበር፤ ነገር ግን ደቀመዛሙርቱ ክርስቲያን ተብለው ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰየሙት በአንጾኪያ በማርቆስ እናት በማርያም ቤት እንደነበር ቅዱስ መጽሀፍ ይነግረናል፡፡ (የሐዋ 11፡26)

በምድራችን በሺዎች የሚቆጠሩ ሃይማኖቶች ይገኛሉ፡፡ የሃይማኖታቸውን መስራች ስናጠና ግን ሰዎች ሆነው እናገኛለን፡፡ ትምህርታቸው ዛሬም በተከታዮቻቸው ይኑር እንጂ እነርሱ ግን በህይወት የሉም፤ የክርስትና ዋና መስራች ግን ትናንት የነበረ ዛሬም ያለ ወደፊትም ዓለምን አሳልፎ የሚኖር ዐልፋና ዖሜጋ ዘዓአለማዊ በመሆኑ ዛሬም ስራውን አላቆመም ማለት ነው፡፡ ክርስቲያናዊ ህይወት ለመኖር ክርስቲያኖች የሚከተለውን መተግበር እንዳለብን የህይወት ምንጭ የሆነው መጽሀፍ ቅዱስ ያስተምረናል፡፡

1. እግዚያብሔርን ማወቅ

መቼም ዓለም አንድ መንደር በሆነችበት ዘመን ስለ እግዚያብሔር ያልሰማ አለ ብሎ ለመናገር ያስቸግራል፡፡ ይሁን እንጂ ከዕውቀት ብዛት እግዚአብሄርን የካዱ (እግዚአብሔር የለም) ያሉ በርካታ ሰዎች በምድራችን መኖራቸው ግልጽ ነው፡፡ ይህም ስንፍና እንጂ እውቀት እንዳልሆነ ልበ አምላከ ቅዱስ ዳዊት ይነግረናል፡፡ “ይበል አብድ በልቡ አልቦ እግዚአብሔር” ሰነፍ በልቡ እግዚአብሔር የለም ይላል (መዝ 13፡1)፡፡ ፍልስፍና ማለት ጥበብን ማፍቀር ማለት እንጂ እግዚአብሄርን አለማወቅ ወይም መካድ ማለት አይደለም፡፡ አንድ ልጅ አባቱን አላውቅህም አባቴ አይደለህም ስላለው አባቱ አልወለደውም ማለት አይደለም እንዳውም ልጁ ሲጠራ አባቱን የካደ ልጅ ተብሎ ይጠራል፡፡

እግዚአብሄርን ማወቅ፡-

ትርጉም ያለው ሕይወት ይሰጣል

በምድራችን ትርጉም ያለው ሕይወት ማለት ምን አልባት የሚመስለን ሀብት፤ ንብረት፤ ስልጣን ፤ ጥሩ መልበስ፤ ጥሩ መመገብ ፤ ጥሩ ቤት መኖር ሊመስል ይችላል፡፡ ነገር ግን ትርጉም ያው ህይወት መኖር የሚቻለው እግዚአብሄርን ሲያውቅ ነው፡፡ በዚህ ዘኪዎስ ጥሩ ምሳሌ ይሆናል፡፡ ዘኪዎስ ጌታውን ሳያውቅ የኖረበት ዘመን ትርጉም አልባ ህይወት ነበር አምላኩን ሲያውቅ ግን “ጌታ ሆይ ካለኝ ሁሉ እኩሌታውን ለድሆች እሰጣለሁ ማንንም በሃሰት ከስሼ እንደሆንሁ አራት እጥፍ እመልሳለሁ አለው” (ሉቃ 19 ፤9) በማለት አዲሱ ክርስቲያናዊ ህይወት ምን እንደሚመስል ነግሮናል፡፡

ታሪክን ይቀይራል

ሰዎች እግዚአብሄሔርን ሲያውቁ ዘማዊ የነበረው ድንግል፤ ዘረኛና ወገንተኛ የነበረው ሁሉን በክርስቶስ አንድ አድርጎ የሚያይ ፍትሃዊ፤ አሳዳጅ የነበረው ስለ ክርስቶስ ተሳደጅ፤ ክፉ የነበረው ደግ፤ ዘፋኝ የነበረው ዘማሪ፤ ነፍሰ ገዳይ የነበረው የሰውን ህይወት የሚያድን ወዘተ ይሆናል፡፡ለዚህ ቅዱስ ጳውሎስ ጥሩ አስረጅ ይሆናል፡፡

2. በዕምነት ማደግ

ብዙዎች ክርስቲያን ተብለው ይጠራሉ ጥቂቶች ብቻ በእምነት ውስጥ በጥበብ ይኖራሉ፡፡ “ዕምነት ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የሚያስረግጥ የማናየውንም ነገር የሚያስረዳ ነውና” (ዕብ11፡1) የሰው ልጅ በሃይማኖት ካልኖረ ለምኞቱ ገደብ የለውም፡፡ ያለኝ ይበቃኛል አይልም፡፡ አመንዝራ ሲያይ በፍትወት ስሜት ይቃጠላል፣ የወይን ጠጅ በብርሌ ባማረ መልኩ ባየ ጊዜ መጠጥ ያምረዋል ለዚህ እኮ ጥበበኛው ጠቢቡ ሰለሞን “ከተማን ከመግዛት ራስን መግዛት ይበልጣል ያለው”

3. በእግዚአብሔር ፍቃድ መኖር

እግዚአብሔር ከእኔ ይልቅ ስለ እኔ ያስባል ብሎ ማመን ነው፡፡የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚያደርግ ለዘለዓለም ይኖራል፡፡(የሐ2፡17) የጌታችንም ፈቃድ ሁሉ የእግዚአብሔር እንደሆነ ሲያስተምር “አባት ሆይ ብትፈቅድ ይህችን ጽዋ ከእኔ ውሰድ ነገር ግን የእኔ ፍቃድ አይሁን የአንተ እንጂ”(ሉቃ22፡42) ምክንያቱም ሀዋርያው እንደተናገረው ”ስለ በጎ ፈቃድ መፈለግንም ማድረግንም በእናንተ የሚሰራ እግዚአብሔር ነውና” እንዲል (ፊሊ1፡13)

4. እግዚአብሔርን መምሰል

ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህች ዓለም ሶስት ዓመት ከሶስት ወራት በአገልግሎት ሲቆይ በርካታ ትምህርቶችን ከማስተማሩም በላይ በሕይወቱ አብነት ለመሆን መልካም ሥራ ካደረገ በኋላ ከመዝ ግበሩ እናንተም እንዲሁ አድርጉ(ዮሐ13፡14)(ምንም እንኳን መልካምነት የባህርይው ቢሆንም) በማለት ክርስቲያኖች በሕይወት ዘመናቸው ክርስቶስን መምሰል እንዳለባቸው መጽሀፍ ይስተምረናል፡፡ሐዋሪያው ቅዱስ ጳውሎስም ይህንን ቃል ”እኔ ክርስቶስን እንደምመስል እኔን ምሰሉ”(1ኛቆሮ 11፡1) በማለት ያረጋግጥልናል፡፡በመሆኑም የመንፈስን ፍሬ በማድረግ የስጋን ሥራ በመተው አምላካችንን መምሰል ይገባናል ማለት ነው፡፡(ገላ 5፡18)ይህንን በማድረግ ቅዱሳን ቅድስናን ገንዘብ አድርገዋል፡፡“እግዚአብሔር መምሰል ግን ለአሁኑ እና ለሚመጣው ተስፋ ስላለው ለነገር ሁሉ ይጠቅማል”(2ጢሞ 4፡8)

5. ፍቅር ሊኖረን ይገባል

በክርስትና መጀመሩያውም መጨረሻውም ፍቅር ነው፡፡ ምክንያቱም “ፍቅር የሌለው እግዚአብሔርን አያውቅም፡፡እግዚአብሔር ፍቅር ነውና” (1ዮሐ 4፡8) በመሆኑም ያለ ፍቅር ክርስትና የለም፡፡ቢኖር እንኳን ቅ/ጳውሎስ እንደተናገረው ከንቱ ነው “ሁሉ ቢኖረኝ ፍቅር ግን ከሌለኝ ከንቱ ነኝ”(1ቆሮ 13፡1)

6. ከመስቀሉ መካፈል

የጠፋውን በግ ፍልጋ ራሱን ባዶ ያደረገው ክርስቶስ (ፊሊ 2፡8) ድሉ በመስቀል ስለ ተጠናቀቀ ክርስቲያኖች በሕይወት ዘመናቸው ከመስቀሉ ተካፋይ መሆን አለባቸው፡፡ ለዚህም ከመስቀሉ ስር የተሰጠችንን እናት ቅድስት ድንግል ማርያምን መውሰድ፤ የተቆረሰውን ቅዱስ ስጋ መብላት፤ የፈሰሰውን ክቡር ደም መጠጣት ይኖርብናል ማለት ነው፡፡ (ዮሐ 19፡27፤ ዮሐ 6፤56) ይህ ሁሉ ሲሆን ለዘለዓለም በሕይወት እንኖራለን ማለት ነው፡፡

ስብሃት ለእግዚያብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለ መስቀሉ ክቡር አሜን
ሰባቱ ምስጢራተ ቤተ ክርስቲያን

ምሥጢር ማለት ቃሉ የግሪክ ቋንቋ ሆኖ ቃሉ ከግዕዝና ከአማርኛ በቀጥታ የተወረሰ ሲሆን ትርጉሙም ድብቅ ፣ ስውር፣ ሽሽግ፣ ረቂቅ ፣ ለቅርብ ዘመድ ካልሆነ በቀር የማይገለጥ ማለት ነው፡፡ ለሁለት የሚከፈል ሲሆን ይኸውም የፍጡር ሚሥጢርና የፈጣሪ ሚስጥር በመባል ይታወቃል፡፡ የፍጡር ምስጢር ሁለት ይዘት አለው፡፡ የሰውና የመላዕክት ምስጢር ይባላል፡፡

በቤተክርስቲያን ውስጥ የሚገኘው የፈጣሪ የእግዚአብሔር ሚስጥር ይህ የከበረ የተወደደ የሚናፈቅ የበረከት ስጦታ ነው፡፡ ብርሃነ አለም ሀዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ እንዲህ ሲል በከበረ ቃሉ ገልፆታል፡፡ “እርሱንም ሳታዩት ትወዱታላችሁ አሁንም ምንም ባታዩት በእርሱ /በክርስቶስ/ አምናችሁ የእምነታችሁን ፍጻሜ እርሱን የነብሳችሁን መዳን እየተቀበላችሁ በማይናገርና ክብር በሞላበት ሀሴት ደስ ይበላችሁ”፡፡ በማለት ስውር ረቂቅ ከሆነው ጸጋ እግዚአብሔር የምንሰጠው ሀብት መሆኑን በማብራራት ገልፆታል፡፡ በዚህ መሰረት በቤተክርስቲያናችን ውስጥ ከሚፈጸሙት ሚስጥራት በቁጥር 7 ተወስነው ተቀምጠዋል፡፡ ውሳኔነታቸው ለሰባቱ ሰማያት ስብዐተ እግዚአብሔር ለማይከፈልባቸው ከተሞች ገላጭ ናቸው፡፡

እነዚህ ሰባት ሚስጥራት ቤተክርስቲያን የሚስጥርነታቸው ምክንያት በአይናችን ልናያቸው በእጃችን ልንዳስሳቸው የማንችል ልዩ ልዩ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች በእነዚህ ሚስጥራት አማካኝነት የሚሰጡን ስለሆነ ነው፡፡ አበው ሲናገሩ በንባብ የተሰወረ ብሂል ምስጢር ይባላል ብለው ስውርነቱን ረቂቅነቱን ይናገራሉ፡፡ ሰባቱ ሚስጥራተ ቤተክርስቲያን የሚባሉት እንደሚከተለው ይዘረዘራሉ፡፡

1. ጥምቀት 2. ሜሮን 3. ቁርባን 4. ክህነት 5. ንስሀ 6. ቀንዲል 7. ተክሊል ናቸው፡፡
1. ሚስጢረ ጥምቀት

ይህ ምሥጢረ ጥምቀት ከኃጢያት ነፃ የምንሆንበት ከዲያቢሎስ አገዛዝ አርነት የምንወጣበት ከእግዚአብሔር በጸጋ የምንወለድበት የምስጢር አይነት ነው፡፡ በቅሰዱሳት መጻህፍት እንደተገለጸው በነብየ እግዚአብሔር በቅዱስ ሕዝቅሌል ት.ሕዝ 36፡25 “ጥሩ ውሀንም ጥምቀትን እረጫችኋለሁ፡ እናንትም ትጠራላችሁ ከርኩስነታችሁም ሁሉ ከጣኦቶቻችሁ ሁሉ አጠራችኋለሁ አዲስ ልብ እሰጣችኋለው” በማለት የዚህን ምስጢር ክብርነት በረከትነት አምልቶ አስፍቶ ተናገሯል፡፡ በዚህ ሀሳብ ሌሎች ንፁሐን አበው ሀዋርያት ተባብረውታል፡፡

በምልአት ሰብከውታል፡፡ የሐዋ.2፡38 ፣ 1ቆሮ 6፡11 ፣ ዮሐ. 3፡5 ፣ ኤፌ 5፡26 ፣ ገላ 3፡27 ፣ ቲቶ 3፡5 ጥምቀት ዳግመኛ ተወልደን ወደ እግዚአብሔር መንግስት የምንገባበት ምስጢር ነው፡፡ ከመጸሕፍ ቅዱስ ውስጥ ጥምቀት ብዙ ምሳሌዎች ይኖሩታል፡፡

እነሆ ከማየአይኅ የዳነበትን መርከብ ቅዱስ ጴጥሮስ የጥምቀት ምሳሌ እንደሆነ ገልጾታል፡፡ 1ኛ ጴጥሮስ 3፡21 ምዕመናን ከሐጢያት ከጥፋት የሚድኑት በጥምቀት ነውና ቅዱስ ጳውሎስም እስራኤል ከግብጽ የባርነት ቀንበር ተላቀው የኤርትራን ባህር ተሻግረው ወደምድረ ርስት ያደረጉትን ጉዞ የጥምቀትን ምሳሌ አድርጎ አመስጥሮታል፡፡ 1ኛ ቆሮ 10፡1-2 ምዕመናን ባህረ ኃጢያትን ተሻግረው ምድረ ርስተ መንግስተ ሰማያትን የሚወርሱት በጥምቀት ነውና፡፡ ዳግመኛም ይህ ብርሃናዊ ሐዋርያ ጥምቀትን በሞትና በመቃብር ይመስለዋል፡፡ ሮሜ 6፡3-4 ቆላ 2፡12 በሞት ጊዜ ነፍስና ስጋ እንደሚለያዩ በጥምቀትም አሮጌው ሰውነት ይሞታል ይቀበራል አዲስ ሰውነት አዲስ ሕልውናን ይጀምራልና፡፡

2. ምስጢረ ሜሮን

ይህ ቃል የጽርዕ ቋንቋ ነው ትርጉሙም መአዛ ያለው የሚያውድ ፣ የሚጣፍጥ፣ ልብ የሚመስጥ ፣ ጣዕም ያለው መልኩ ጽርየቱ ዘይት ነው፡፡ በግዕዝ ቅብዕ፣ ቅብዐ ሜሮን ይባላል፡፡ ከብዙ እጽዋት ተቀምሞ የሚሰራ ነው፡፡ ሕዝበ እስራኤልን የሚያስተዳድሩ የእግዚያብሔር እንደራሴዎች ነገስታትን መሲሀን የሚባሉት ለዚህ ቅብ ተቀብተው ስለሚነግሱ ነው፡፡ ዘፍ 20፡23 1ኛ ሳሙ 10፡1 ዘዳ 28፡41 1ኛ ሳሙ 9፡6 1ኛ ነገስት 1፡34 ይህ ብቻ አይደለም እግዚአብሔር የሚገለገልባቸው የቤተመቅደስ ነዋያተ ቅድሳትን አስቀድሞ በዚህ መታተም አለባቸው፡፡ ከተቀቡ በኋላ ለቤተ መቅደስ እንጂ ለተራ አገልግሎት አይውሉም ስለ ቅብዐ ሜሮን ቅዱስ መጽሐፍን የፃፉ ሰዎች የመንፈስ ቅዱስን ስጦታ ቅብዐት ይሉታል፡፡ 2ኛ ቆሮ 1፡21 ዮሐ 2፡20 ቅብዕን በመንፈስ ቅዱስ ማህተምን ይሉታል፡፡ ኤፊ 1፡13 ፣4፡30 ይህ ቅብዓ ማህተመ ሕይወት በመሆኑ ለአገልግሎት ይውላል፡፡

3. ምሥጢረ ቁረባን

ይህ ቃል የሱርስት ቃል ነው፡፡ ትርጉሙም አምኃ ስጦታ ማለት ነው፡፡ ሥጋውና ደሙ የተሰጠን በነፃ ያለ ዋጋ ሳይገባን በችሮታ ነውና፡፡ በቤተክርስቲያን ምሥጢራት ሁሉ መደምደሚ ቅዱስ ቁርባን ነው፡፡ መስዋዕት ማቅረብ የተጀመረው በአዳም ጊዜ ሲሆን ከአዳም እስከ ሙሴ የተነሱ አበው ሁሉ በህገ ልቦና ለእግዚአብሔር መስዋት ይሰው ቁርባን ያቀርቡ ነበር፡፡ መስዋዕታቸው ከእንሰሳ ቁርባናቸው ከእህልና ከአትክልት ማለት ከስንዴ እህል፣ ከወይን ፍሬ የሚቀርብ ነው፡፡ ዘመነ ኦሪት በብሉይ ኪዳን በሙክራብ የተሰዋ እንሰሳት ሁሉ በአዲስ ኪዳን በቤተክርስቲያን ለሚሰዋው ሁሉ የክርስቶስ ሥጋና ደም ምሳሌ ነበር፡፡ መልከ ጼዴቅ ያበረከተው ኅብስተ አኮቴት ጽዋዐ በረከት ለአምላክ የሥጋውና የደሙ ምሳ ሆነው አልፈዋል፡፡ ከምሥጢራት አንዱ መሆኑ ሕብስቱ ተለውጦ የክርስቶስ ሥጋ ጽዋው ተለውጦ የክርስቶስ ደም ሲሆን አይታይም፡፡ ነገር ግን እምነት ያለው ሁሉ በእምነት መነጽር ይመለከተዋል፡፡ ይህ ሳይሆን ሳይታይ የሚወደድን ሕይወት ለማግኘት ከቁርባን በፊት ንስሐ መግባት ለአስራ ስምንት ሰዓት መጾም አለበት፡፡ ንጽሕናውን በጠበቅ አለበት፡፡ መምክረ ካህን ጸንቶ መገኘት ያስፈልጋል፡፡

4. ምሥጢረ ክህነት

ይህ ቋንቋ የግዕዝ ቋንቋ ነው፡፡ ተክህነ አገልገለ ከሚለው ግስ የወጣ ነው፡፡ ክህነት የተጀመረው በአባታች አዳም ነው፡፡ ክህነት የአገልግሎት ስም ሆኖ የቤተክርስቲያን ከፍተኛ መንፈሳዊ ማዕረግ ነው፡፡ እግዚአብሔር አዳምን ፈጥሮ በልጅነት አክብሮ ነብይና ካህን አድርጎ ሾሞ በኦሪት በወንጌል ሥርዓት እስኪወሰን ድረስ ከአዳም ጀምሮ እስከ ሙሴ የነበሩ አበው በበረከት አበው ከእግዚአብሔር እየተሾሙ ትንቢትን ክህነት ከቅዱሱ መንፈስ እየተቀበሉ (እየተሾሙ) በነብይነታቸው ያለውን የሚመጣውን ሲገልጽ ሲያስተምሩ በሀብተ ክህነታቸው መስዋዕት ሲቀርቡ ነበር፡፡ ክህነት በዘመነ ኦሪት ለሌዊ ነገድ ከተሰጠ በኋላ ሲወርድ ሲወራረድ እስከ ክርስቶስ ደርሷል፡፡ ታላቁ ሊቀ ካህናት እየሱስ ክርስቶስ እንደ ብሉይ ኪዳን መስዋዕት እንሰሳ ሳሆን እራሱን መስዋዕት፣ እርሱ ሰዋዒ ሆኖ ወደ መቅደስ ገብቷል፡፡ ዮሐ 20፡22 ማሬ 18፡18 1ኘና ቆሮ 4፡1 ማሬ 28፡20

5. ምሥጢረ ንስሐ

ይህ ቃል የግዕዝ ቃል ነው፡፡ ትርጉሙም በሰሩት ኃጢያት መጸጸት ምነው ባልሰራሁት ባላደረኩት ብሎ ማልቀስ ወደ ኃጢያት ላለመመለስ መወሰን፣ በሕጉ ጸንቶ ለመኖር ቃል መግባት፡፡ ክርስቲያን በጥምቀት ከአለም ክፉ ስራዎች ሁሉ የተለየ ነው፡፡ ህይወቱ ለክርስቶስ የተሰጠ ነው፡፡ ሮሜ 12፡1 የመጨረሻው ግቡና ዓላማው ሥርየተ ኃጢያትን ማግኘት እና የዘላለም ሕይወት መወረስ ነው፡፡ አካሉ የመንፈስ ቅዱስ ነው፡፡ 1ቆሮ 6-19

6. ምሥጢረ ቀንዲል

ይህ ቃል የላቲን ቋንቋ ነው ትርጉሙም ፍፁም መብራት ማለት ነው፡፡ ከሰባቱ ሚስራት አንዱ ቀንዲል ነው፡፡ በብሉይ ኪዳን ዘይት የፈውስ ምልክት ነው፡፡ በደዌ ዳኛ በአልጋ ቁራኛ ተይዘው የሚሰቃዩ ህሙማን ወይም በድንገተኛ አጋጣሚ የመቁሰል አደጋ የደረሰባቸው ቁስለኞች እየተቀቡ ይፈወሱ ነበር፡፡ ኢሳ 1፡6 ሉቃ 10፡34 ራዕ 3፡18 ማር 6፡13 ይህ ቅብዓተ በሐዲስ ኪዳን ለሚጠመቁ ከሚደረግ ቅብዐ ሜሮን ጋር ግንኙነት የለውም ራሱን የቻለ ሕሙማነ ሥጋ ብቻ ሳይሆን ሕሙማነ ነፍስ ኃጥአን የሚቀቡት ፈውስ የሚያገኙበት ነው፡፡ ማር 6፡13 ያዕ 5፡13-15 ራዕ 1፡17፡፡

7. ምሥጢረ ተክሊል

ይህ ማለት “ተከለለ” ተቀናጀ ከሚለው የግዕዝ ግስ የተገኘ ነው፡፡ በሥርዓተ ጋብቻ ቅደም ተከተል መሰረት በመተጫጨት እና በቃል ኪዳን የተመሰረተ ጋብቻ በተክሊል ይፈጸማል፡፡ ቤተክርስቲያን ምስክርነት የሚፈጸመው ጸጋ መንፈስ ቅዱስን የሚያሰጥ ስለሆነ ነው፡፡ ክርስቲያናዊ ጋብቻ ትክክለኛነቱም የሚታወቀው በተክሊል ሥጋወ ደሙ ሲፈጸም ነው፡፡ ክርስቲያናዊ ጋብቻ ትክክለኛነቱም የሚታወቀው በትክሊል ሥጋወ ደሙ ሲፈጸም ነው፡፡ ዘፍ 1፡27-28 ፣ 2-18 ማቴ 19-4 እነዚህን ምሥጢራተ ቤተክርስቲያን አውቀን ተረድተን የእምነታችን ፍጻሜ የሆነውን አምላካችንን ለተፈጠርንለት ዓላማ በመገዛት የነፍሳችንን መዳን ልናረጋግጥ ይገባል፡፡ ለዚህም ቸሩ አምላካችን እግዚአብሔር እንዲረዳን የወላዲተ አማላክ አማላጅነት እንዳይለየን የጻድቃን ፀሎት የቅዱሳን በረከት እንዳይለየን ፈቃዱ ይሁንልን አሜን!!!

ወስብሃት ለእግዚያብሔር!