ትምህርተ አፁዋማት

ትምህርተ አፁዋማት

በስመ አብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ አሜን!

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አጹዋማትን መሠረት ባደረገ እውቀትን ለማስፋፋት ትምህርት ለምእመናኑ ማዳረስ በጣም አስፈላጊ ነው። የተዋሕዶ ትምህርት በእለተ ቅዳሴ ብቻ በሚሰጡ ቃለ እግዚያብሄር ተዳሶ የሚያልቅ ሳይሆን የእለተ ተእለት መንፈሳዊ ምግባችን ሊሆን ይገባል።

ለዚህም ሲባል በዚህ ክፍል ውስጥ ስለ አጹዋማት በየጊዜው ለምእመናኑ ትምህርት ለማዳረስ የሚሞከር ይሆናል።

ይሁንና በዚህ ዝግጅት ግን እንደ ትምህርቱ ጥልቀትና ምጥቀት ሳይሆን፣ እንደ አዘጋጁ የዕውቀት ውሱንነትና እንደ ተቀባዩ የአእምሮ ስፋት መጠን፣ ግልጽ በሆነ አቀራረብ ይቀርባል።